በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራናዊዋ የሴቶችና የስብዓዊ መብት አቀንቃኝ የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆነች


ፎቶ ፋይል፦ ኢራናዊዋ የሴቶችና የስብዓዊ መብት አቀንቃኝ፣ ናርገስ ሞሃመዲ
ፎቶ ፋይል፦ ኢራናዊዋ የሴቶችና የስብዓዊ መብት አቀንቃኝ፣ ናርገስ ሞሃመዲ

በእስር ላይ ያለችው ኢራናዊዋ የሴቶችና የስብዓዊ መብት አቀንቃኝ፣ ናርገስ ሞሃመዲ የዚህ ዓመት የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆናለች፡፡

ናርገስ ሞሃመዲ፣ በኢራን መንግስት 13 ግዜ ተይዛ፣ 5 ግዜ ጥፋተኛ ስትባል፣ የ31 ዓመት እስር እና 154 ግርፋት እንዲፈጸምባት ተወስኖባታል።

ባለፈው ዓመት፣ ማሳ አሚኒ የተባለች ሴት፣ ’የፊት ሽፋን ልብስ በተገቢው መንገድ አላደረግሽም’ በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሳለች ሕይወቷ ማለፉን ተከትሎ በኢራን ለተነሳው ተቃውሞ፣ ናርገስ ሞሃመዲ ከእስር ቤት በመሆን ድጋፏን ሰጥታ ነበር።

  • ናርገስ ሞሃመዲ ለሰብዓዊ መብት ትግል የጀመረችው በእ.አ.አ 1990ዎቹ ሲሆን፣ በመጀመሪያ የተያዘችው በ2011 ከታሰሩ ሌሎች አቀንቃኞች እና ቤተሰቦቻቸው ጋር በመሥራቷ ነበር።
    ተጨማሪ ሰዎች በታሰሩ ቁጥር፣ ጥንካሬያችን ይጨምራል”

በኋላም በኢራን የሚተላለፈውን የሞት ቅጣት፣ ሰቆቃ እና በፖለቲካ እስረኖች ላይ የሚፈጸምን ጾታ ላይ ያተኮረ ግፍ በመቃወሟ ለበርካታ ግዜያት ተይዛለች፡

የእስር ቤት ባለሥልጣናት ጎብኚዎች እንዳታገኝ እና ስልክ እንዳትቀበል ቢያደርጉም፣ የአሚኒን ሞት አንደኛ ዓመት በማስመልከት አሾልካ ያወጣችው ጽሁፍ በኒው ዮርክ ታይምስ ላይ ታትሟል።

“ተጨማሪ ሰዎች በታሰሩ ቁጥር፣ ጥንካሬያችን ይጨምራል” ስትል ጽፋለች ናርገስ ሞሃመዲ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG