የዘንድሮው የዓለም የኤድስ ቀን የታሰበውና ፀረ-ኤድስ እንቅስቃሴዎቹም የሚካሄዱት “ዜሮ ማግለል፣ ዜሮ በኤችአይቪ መያዝ፣ ዜሮ የኤድስ ሞት” በሚል መርኅ ነው፡፡
ይህ በመጭዎቹ ሃያ አምስት ወራት ውስጥ፣ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር እስከ 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ መጨበጥ ይቻላል ተብሎ የተቀመጠ ግብ ነው፡፡ “ይቻላል?” …
ዛሬ በመላው ዓለም ከአንድ ሺህ በላይ ሕፃናት ከኤችአይቪ ጋር ይወለዳሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ግማሽ የሚሆኑት ሁለተኛ ዓመት የልደት ቀናቸውን አያዩም፡፡
ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ ከሚገኝ ሕፃናት ከዘጠና ከመቶ በላይ የሚሆኑት ቫይረሱን የሚያገኙት ከእናቶቻቸው ነው፡፡
ዛሬ መድኃኒት አለ፤ ተቋማትም እየተበራከቱ ነው፡፡
ለመሆኑ የኢትዮጵያ አያያዝና አካሄድ፣ ተስፋዋስ ለነገዎቹ ሰዎች ምን ይመስላል?
አቶ ዓለሙ አኖ፣ በኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት የዘርፈ-ብዙ ምላሽ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር፤ አቶ ደረጀ ዓለማየሁ፣ ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሰዎች ማኅበራትና መረቦች መረብ ዋና ዳይሬክተር፤ አቶ መንግሥቱ ዘመነ፣ የአንጋፋውና በኢትዮጵያ ከግዙፎቹ ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሰዎች ማኅበራት አንዱ የሆነው የመቅድም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ዶ/ር አጎናፍር ተካልኝ፣ ለኤችአይቪ/ኤድስ የሚሰጠው ምላሽ ቀዳሚ ተሣታፊ፣ መሪና ተሟጋች፣ እንዲሁም አሁን የኢትዮጵያ የወባ መከላከያና መቆጣጠሪያ ኮንሰርቲየም ዋና ዳይሬክተር በውይይቱ ውስጥ ይሣተፋሉ፡፡
ያዳምጡት፡፡