አዲስ አበባ —
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን በዓመት አንድ ጊዜ የሚከበር የወጣቶች ቀን እንደሚኖረው ተገለፀ፡፡
በአባይ ጉዳይ ላይ ሁሉም ወገኖች ተጠቃሚ የሚሆኑበት መፍትሔ እንዲገኝም የኅብረቱ ኮሚሽን ፍላጎት እንደሆነ ኮሚሽነሯ ተናግረዋል፡፡
የሕብረቱ ኮሚሽነር ን’ኮሣዛና ድላሚኒ-ዙማ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “በአዲስ አስተሳሰብ ስሜትና መንፈስ ሁሉም ወገኖች አሸናፊና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ግልፅ ንግግር መጀመር አስፈላጊ ነው፡፡ በቅኝ አገዛዝ ኃይሎች ግንዛቤና አካሄድ ሣይሆን በመላ-አፍሪካዊነትና በአፍሪካ ኅዳሴ ስሜትና መንፈስ ነው ንግግሮቹ መካሄድ ያለባቸው” ብለዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የመለስካቸው አምሃ ዘገባ ያዳምጡ፡፡