በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጀሪያ ምርጫ ውጤት


ናይጄሪያውያን ባለፈው ቅዳሜ ባካሄዱት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየገባ ያለው የድምፅ ውጤት እንደሚያሳየው ሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ እየመሩ ናቸው። ዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ ግን የድምፅ ቆጠራ ውጤቱን የተሳሳተና ተቀባይነት የሌለው በማለት ውድቅ አድርጓል።

ትናንት የናይጄሪያ ነፃው ብሄራዊ የምርጫ ኮሚሽን በሰጠው መግለጫ ቡሃሪ ቢያንስ በስድስት ክፍላተ ሃገር ዋናው ተፎካካሪያቸው አቲኩ አቡበከር ደግሞ በፌዴራል ካፒታል ክፍለ ግዛት እንዳሸነፉ ገልፅዋል።

የአቲኩ አቡበከር ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኡቼ ሴኮንደስ በበኩላቸው ፓርቲያቸው በናሳራዋ ክፍለ ሃገር እና በዋና ከተማዋ የድምፅ ቆጠራ መዛባት እንዳለ ደርሶበታል ብለዋል።

አቡጃ ላይ በተካሄደ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲናገሩ የቡሃሪ መንግሥት ከምርጫው ኮሚሽን ጋር ተመሳጥሮ በሀገሪቱ ዙሪያ በሚገኙ የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ድምፅ ቆጠራ እንዲዛባ እያደረገ ነው ሲሉ ወንጅለዋል። እኛ ደግሞ ትክክለኛውን የድምፅ ውጤት ከየምርጫ ጣቢያው ይዘናል ሲሉም አክለዋል። በናይጄሪያ በሰላሳ ስድስቱም ክፍላተ ሃገር እና በፌዴራል መዲና ክፍለ ግዛት በጠቅላላ ምርጫው የተካሄደ ሲሆን በእያንዳንድ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ በተዛባባቸው አካባቢዎች እንዲዘገይ ተደርጓል።

ከሰባ የሚበልጡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን ያቀፈው “ዘ ሲቹዌሽን ሩም” የተሰኘው ቡድን እንዳስታወቀው ከምርጫው በተያያዙ ሁከቶች ቢያንስ ሰላሳ ዘጠኝ ሰው ተገድሏል።

የምርጫ ኮሚሽኑ “በአንዳንድ አካባቢዎች ድምፅ አሰጣጡ እንዲዘገይ ቢደረግም በምርጫው አፈጻጸም በአጠቃላዩ ረክተናል ማለታቸውን የፈረንሳይ የዜና ወኪል ዘግቧል።

በናይጄሪያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ስቱዋርት ሲሚንግተን ትናንት ሰኞ ባወጡት መግለጫ ህዝቡ ብሄራዊ የምርጫ ኮሚሽኑ የድምፅ ውጤቶችን አጠናቅሮ ይፋ እስከሚያደርግ በትዕግስት እንዲጠብቅና ከሁከት እንዲቆጠብ ጥሪ አቅርበዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG