በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያውያን ብሔራዊ የኃዘን ቀን እያሰቡ ነው


ናይጄሪያውያን በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ በአደባባዮችና በየመሥሪያ ቤቶቹ ሜዳዎች ተሰባስበው፣ የመጀመሪያውን ብሔራዊ የኃዘን ቀን እያሰቡ መሆናቸው ተነገረ።

ናይጄሪያውያን በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ በአደባባዮችና በየመሥሪያ ቤቶቹ ሜዳዎች ተሰባስበው፣ የመጀመሪያውን ብሔራዊ የኃዘን ቀን እያሰቡ መሆናቸው ተነገረ።

ይህ ሳይታሰብ ድንገት የተካሄደ የኃዘን ቀን፣ የመንግሥቱን ኦፊሴላዊ ዕውቅና እንዳላገኘም ታውቋል። ስብስቡ የተመራው በሲቪሉ ማኅበረሰብ የመብት ተሟጋቾች ሲሆን፣ ዓላማውም «በመላው ናይጄሪያ እየተስፋፋ ነው» ያሉትን አመፅና ግጭት ለመቃወም እንደሆነ ተመልክቷል።

በሀገሬው አቆጣጠር ከቀኑ በ6 ሰዓት ላይ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ናይጄሪያውያን፣ ዘመዶችና ወዳጆቻቸውን በእርስ በርስ ግጭት፣ በጦርነትና በሽብርተኞች ካጡ ቤተሰቦች ጋር ሆነው፣ የፅሞና ጊዜ ማሳለፋቸውና የሞቱትንም ማሰባቸው ታውቋል።

አቡጃ ውስጥ የሕዝባዊ ጤና አገልግሎት ባለሞያው ፍሌክስ አብርሃም፣ ዕለቱ የሚያሳዝን ትውስታ ቢኖረውም፣ ለናይጄሪያ ግን እጅግ አስፈላጊ ቀን እንደሆነ ተናግረዋል።

«የግድያው መጠን ከቀን ወደ ቀን እያየለና እየጨመረ በመምጣቱ፥ ብዙዎቻችን ናይጄሪያውያን በህመሙ ደንዝዘናል» ሲሉ ቃላቸውን ለቪኦኤ የሰጡት እኒሁ የጤና ባለሙያ፣ «ቁጥሩ ብቻ ነው የሚታወሰን፤ ለምሳሌ ሃያ ሞቱ፣ ወዘተ። ነገር ግን እነዚህ የሚገደሉ ወገኖቻችን ስም፣ ቤተሰብ፣ ሙያ፣ ማንነት አላቸው» በማለት፣ የብሔራዊ የኃዘን ቀኑን አስፈላጊነት አስገንዝበዋል።

በሌላ እንደ ደቡብ አፍሪካ፣ ብሪታንያ እና ዩናይትድ ስቴትስ ኒሬኢ በሆኑ ናይጄሪያውያን ዘንድም ዕለቱ እንዲታሰብ ዕቅድ ተይዟል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG