የናይጄሪያ ሕግ አውጭዎች፣ በስርቆት ተወስዶ ለቻይና ተሽጧል፤ የተባለውን 2ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ነዳጅ ጉዳይ እየመረመሩ ነው፡፡ ባለሥልጣናትም፣ በነዳጅ ስርቆት በየዓመቱ የሚደርሰውን የቢሊዮን ዶላር የነዳጅ ኪሳራ ለማቆም እየታገሉ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡
የተወካዮች ምክር ቤት የነዳጅ ስርቆት ምርመራ ጊዜያዊ ኮሚቴ፣ እአአ በ2015 ተሰርቆ ለቻይና የተሸጠውን፣ የ45 ሚሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ጉዳይ መልሶ ማጣራት ጀምሯል፡፡
ውስጥ አዋቂው እንዳመለከተው፣ የተሰረቀው ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት፣ በበርካታ የቻይና ወደቦች ተከማችቶ ከቆየ በኋላ፣ ቆየት ብሎ፣ በናይጄሪያ ብሔራዊ የነዳጅ ኩባንያ መሸጡን ባለሥልጣናቱ ገልጸዋል፡፡
የድፍድፍ ነዳጅ ዘይቱ፣ ከናይጄሪያ ገቢ ከ90 ከመቶ በላይ የሚኾነውን የሚሸፍን ሲኾን፣ የናይጄሪያ ባለሥልጣናት ለዐሥርት ዓመታት የነዳጅ ስርቆሽን ለመግታት ሲሞክሩ ቆይተዋል፡፡
የነዳጅ ስርቆቱ፣ ናይጄሪያን በየወሩ 700 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያሳጣት ባለሥልጣናቱ አመልክተዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡