በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጄሪያ የጸጥታ ኃይሎች 58 ታጋቾችን አስለቀቁ


የናይጄሪያ የጸጥታ ኃይሎች 58 ታጋቾችን አስለቀቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:31 0:00

የናይጄሪያ የጸጥታ ኃይሎች፣ በዋና ከተማዪቱ አቡጃ አቅራቢያ በምትገኘው በማዕከላዊ ኮጂ ግዛት፣ በታጣቂዎች ታፍነው የተወሰዱ 58 ሰዎችን አስለቅቀዋል፡፡ ታጋቾቹን ለማስለቀቅ በተደረገው እንቅስቃሴ፣ ከታገቱት መካከል አንደኛው መሞቱንና አጋቾቹ ማምለጣቸውን፣ የናይጄሪያ ፖሊስ አመልክቷል፡፡

የፖሊስ ባለሥልጣናት፣ ትላንት እሑድ በሰጡት መግለጫ፣ “የነፍስ አድን ተልዕኮው፥ በፌዴራሉ ዋና ከተማ አካባቢ እና በአጎራባች ግዛቶች፣ የወንጀለኞችን ጥቃት ለመከላከል፣ ታጋቾችን ለመታደግና ወንጀለኞችን ለመያዝ የተካሔደው ዘመቻ አካል ነው፤” ብለዋል፡፡

ታጋቾቹ የተያዙት፣ በማዕከላዊ ኮጂ ግዛት አቅራቢያ በሚገኝ ጌጉ አውራጃ እንደኾነም ተገልጿል፡፡

ፖሊሶቹ ከሥፍራው ሲደርሱ፣ አጋቾቹ ብርቱ ፍልሚያ አድርገዋል፡፡ ይኹንና፣ ከታጣቂዎቹ ይልቅ ዐይለው የተገኙት የጸጥታ ኃይሎቹ፣ አጋቾቹ ታጋቾቹን ጥለው ከመሸሻቸው በፊት ብዙዎቹን እንዳቆሰሏቸው ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የጸጥታ ኃይሎቹ ድንገተኛ ዘመቻ የተካሔደው፣ በአቡጃ አካባቢ የደኅንነት ስጋት እያየለ ከመጣ በኋላ መኾኑ ሲገለጽ፣ ባለፈው ሚያዝያ ወር፣ ከካዋሊ አውራጃ መንደሮች፣ 29 ሰዎች ታግተው መወሰዳቸው ተነግሯል፡፡

/ሙሉ ዘገባው ከፋይሉ ጋራ ተያይዟል/

XS
SM
MD
LG