ጠቅላላ መጠኑ አንድ ሺ ሜትሪክ ቶን የሚጠጋ የምግብ ዕርዳታ እና ሌሎች “አስፈላጊ” ያሏቸውን ቁሳቁሶች የጫኑ 27 የጭነት ተሽከርካሪዎች ባለፈው ሳምንት መቀሌ መድረሳቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አስታወቁ።
“በኢትዮጵያ ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ አሁንም አስከፊ ነው” ያሉት የዩናይትድ ስቴትሷ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት /USAID/ ኃላፊም ላለፈው አንድ ዓመት ተኩል በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደው ግጭት ሰብዓዊ ቀውስ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ውድመት ያስከተለ ነው” ብለዋል። ይሁና የተሻለ ተስፋ የሚፈነጥቁ ሁኔታዎች መታየታቸውንም አመልክተዋል።
ዝርዝሩን ቆንጅት ታዬ ነች ያሰናዳችው።