በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምርጫውን ያሸነፉት አዲሱ የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሆኑ


አዲሱ ፕሬዚዳንት ሂችለማ
አዲሱ ፕሬዚዳንት ሂችለማ

በዛምቢያ ብሄራዊ ምርጫውን ያሸነፉት አዲሱ ፕሬዚዳንት ሂችለማ ከ12 ቀናት ፉክክር በኋላ ሥልጣን ላይ የነበሩትን ኤዳጋር ሉንጉን በማሸነፋቸው የፕሬዚዳንትነቱን ሥልጣን ተረክበዋል፡፡

አዲሱ የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ዛሬ ማክሰኞ በዓለተ ሲመታቸውን በሚያከበሩት ወቅት ከቪኦኤው ዘጋቢ ፒተር ክሎቲ ጋር የአጭር ጊዜ ቆይታ አድርገዋል፡፡

ፕሬዚዳንት፣ በመጭው የሥልጣን ዘመናቸው ከህዝባቸውና ደጋፊዎቻቸው ጋር በመሆን፣ ዝቅተኛውን ምጣኔ ሀብት እንደሚያሻሽሉ፣ የህግ የበላይነትን እንደሚያሰፍኑ፣ የሰብአዊ መብትን እንደሚያከብሩ ከአካባቢው አገሮች ሆነ ከዋሽንግተን ጋር የተሻለ ግንኙነት እንደሚመሰርቱ ተናግረዋል፡፡

ዛሬ በየገበያው ስፍራ፣ በየስራው ገበታና በየትኛውም ቦታ የሚታይ መከፋፈል መኖሩን ገልጸው በሚቀጥሉት 100 ቀናት ውስጥ ለበርካታ ዓመታት ተከፋፍላ የቆየችውን አገራቸውን አንድ ለማድረግ እንደሚሰሩ፣ ተመራጩ የዛምቢያ ፕሬዚዳንት አስታውቀዋል፡፡

“እኛ ራሳችን የዴሞክራሲ ውጤት ነን” ያሉት አዲሱ ፕሬዚዳንት “ብዙ አስቸጋሪ ነገሮችን አልፈን ይኸው ተመርጠናል የዲሞክራሲ ልጆች ስለመሆናቸንም መልዕክት አስተላልፈናል” ሲሉ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG