በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኔዘርላንድስ እና ኢጣልያ በተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት መቀመጫን በየተራ ለመጠቀም መስማማታቸው ተገለጸ


ኔዘርላንድስ እና ኢጣልያ ለሁለት ዓመት የሚዘልቀውን በተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት መቀመጫን በየተራ ለመጠቀም ከብዙ አጨቃጫቂ ክርክር በኋላ በትናንቱ ዕለት መስማማታቸው ተገለጸ።

ሁለቱ የአውሮፓ ሕብረት አባል አገሮች ለምዕራብ አውሮፓና ለሌሎች ቡድኖች የተሰጠውን መቀመጫ በአንዳንድ ዓመት ለመካፈል የቻሉት በ5 ዙር የድምፅ አሰጣጥ ተካሂዶ እኩል 95 ድምፅ ካገኙ በኋላ ነው።

በስምምነቱ መሠረት መቀጫውን ኔዘርላንድስ በቀጣዩ ዓመት በ2017 እአአ ኢጣልያ ደግሞ በ2018 ዓ.ም ይጠቀማሉ ማለት ነው። እንዲሁም ሌሎች መቀመጫ ያገኙ አገሮች ቦሊቭያ፣ ኢትዮጵያ፣ ካዛኪስታን እና ስዊድን ናቸው።

አዲስ የተመረጡትና ጊዜያቸውን በመጪው ታኅሣሥ ወር የሚጨርሱት የምክር ቤት አባላት አንጎላ፣ ማሌዥያ፣ ኒውዚላድ፣ ስፓኛ እና ቬኔዝዌላ ናቸው። አዲሶቹ አባላት ሥራቸውን በመጪው ጥር 1 ቀን ሲጀምሩ፣ ከቋሚ አባላቱ ማለትም ከቻይና፣ ከፈረንሳይ፣ ከሩስያ፣ ከብሪታንያና ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር፣ እንዲሁም ቋሚ አባላት ካልሆኑት ከግብጽ፣ ከጃፓን፣ ከሴኔጋል፣ ከዩክራይንና ከኡሩጋይ ጋርም ይገናኛሉ።

በተጨማሪም መቀመጫ ካገኙት አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ እንደመሆኗ፣ በተመድ የኢትዮጵያ ሚሽን ዶ/ር ተቀዳ ዓለሙ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራርያ ሰጥተዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ኔዘርላንድስ እና ኢጣልያ በተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት መቀመጫን በየተራ ለመጠቀም መስማማታቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:39 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG