በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምርጫ ቦርድ በአንድነትና በመኢአድ ጉዳይ ውሣኔ ሰጠ


የአንድነትና የመኢአድ አርማዎች
የአንድነትና የመኢአድ አርማዎች

የውሣኔው ተቃዋሚዎች “የፖለቲካ ውሣኔ ነው” ብለውታል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:04 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ እንዲሁም መላ ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲዎች ውስጥ አለ ያለውን አለመግባባት ተከትሎ ለፓርቲዎቹ ቀነ ገደብ የቆረጠው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ውሣኔ ሰጥቷል፡፡

በዚህም በአንድነት በኩል በእነ አቶ ትዕግሥቱ አወሉ ለሚመራው ቡድን፤ ከመኢአድ ደግሞ በእነ አቶ አበባው መሃሪ ለሚመራው ቡድን ወስኖ ፓርቲዎቻቸውን መርተው ወደ ምርጫው እንዲገቡ ዕውቅና መስጠቱን ውሣኔውን በንባብ ያሰሙት የቦርዱ ፀሐፊና የፅሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ መርጋ ዱፊሳ አመልክተዋል፡፡

ምርጫ ቦርድ የሰጠው ውሣኔ የፖለቲካ ውሣኔ ነው ሲሉ የመኢአዱ አቶ ማሙሸት አማረና የአንድነቱ አቶ ግርማ ሠይፉ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

ዕውቅና የተሰጣቸው ቡድኖችም ቢሆኑ ችግር ያለባቸው ናቸው ያሉት በውሣኔው ላይ በሂልተን አዲስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ለውሣኔአቸው እንደመሠረት የተጠቀሙት “ከቦርዱ ጋር ጤናማ ግንኙነት ያለው፣ ለቦርዱ ትዕዛዝ ምላሽ የሚሰጥ፣ ቦርዱን የሚያከብር፣ የቦርዱን ገለልተኛነት የሚቀበል” መሆኑን ገልፀዋል፡፡

መግለጫውን የተከታተለው መለስካቸው አምሃ የተቃዋሚዎቹን አስተያየት አክሎ ያጠናቀረውን ዘገባ የያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG