በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኔቶ ኃላፊ ስዊድን ወደ ኔቶ ጥምረት እንድትቀላቀል ቱርክ መደገፏን ገለፁ


የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት(ኔቶ) ስብሰባ
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት(ኔቶ) ስብሰባ

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት(ኔቶ) ስብሰባ "ከመጀመሩ በፊት ታሪካዊ ሆኗል" ሲሉ፣ የጥምረቱ ዋና ኃላፊ ስቶልትንበርግ ተናገሩ። ስቶልትንበርግ ይህን ያሉት ከቱርክ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን ጋር ያደረጉት ንግግር፣ ለወራት መፍትሄ አጥቶ በቆየውና፣ ኤርዶጋን ስቶኮልም የቱርክ መንግስት እንደ ፅንፈኛ የሚመለተውን የፖለቲካ ፓርቲ ቅርጫፍ ለመበተን በቂ እርምጃ አልወሰደችም በማለት ሲወቅሱ የቆዩበት ጉዳይ መልካም እመርታ ካሳየ በኃላ ነው።

ኤርዶጋን ስዊድን የኔቶን ጥምረት ለመቀላቀል ያቀረበችው ጥያቄ በቱርክ ፓርላማ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለመደገፍ ቃል ገብተዋል። ሌላዋ ቀሪ የኔቶ አባል ሀገር የሆነችው ሀንጋሪም በሚስጥር በሚካሄደው የድምፅ አሰጣጥ በተመሳሳይ ሁኔታ ድጋፏን ትሰጣለች ተብሎ ይጠበቃል።

የኔቶ ጉባዔ ዋዜማ ላይ የተወሰደ የመጨረሻ እርምጃ መሆኑ በተገለፀው በዚህ ውሳኔ፣ ኤርዶጋን ከስዊድን ጋር ያላቸውን ጉዳይ፣ አንካራ የአውሮፓ ህብረትን ለመቀላቀል ጠይቃ ምላሽ ካላገኘችበት ጥያቄ ጋር አያይዛዋለች።

የአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት "ዩናይትድ ስቴትስ ሁልጊዜም ቱርክ የአውሮፓ ህብረት አባል ለመሆን ያላትን ምኞት ትደግፋለች፣ አሁንም መደገፏን ትቀጥላለች። የአባልነት ማመልከቻው ጥያቄ ሂደት በአውሮፓ ህብረት እና በቱርክ መካከል ያለ ጉዳይ ነው" ብልዋል።

በዛሬው እለት የጀመረው የኔቶ ስብሰባ የመጀመሪያው ቀን ጉባዔ ሲጠናቀቅ ከኤርዶጋን ጋር ተገናንተው ለመነጋገር ቀጠሮ የተያዘላቸው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ ቱርክ ለስዊድን ድጋፍ የመስጠቷን ዜና በደስታ ተቀብለው "ጠቅላይ ሚኒስተር ክሪስተርሰን አና ስዊድንን 32ኛ የኔቶ አጋር አድርገን ለመቀበል እጓጓለሁ" ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG