በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ድልድይ ተደርምሶ የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ


በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ድልድይ ተደርምሶ የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:51 0:00

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲን ዋናውን ጊቢ ከቴክኖሎጂ ትምሕርት ክፍል ቅጥር ጊቢ ጋር የሚያገናኘው ድልድይ በመደርመሱ በ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በአደጋው ምክንያት በ415 ተማሪዎች ላይ ከከባድ እስከ ቀላል ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉን የሲዳማ ክልል የሠላም እና ፀጥታ ቢሮ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፆዋል፡፡ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ለፈተና የሚቀርቡበት ጊዜ ወደፊት እንደሚገለፅ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው ዕለት መሰጠት የተጀመረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በ130 የመፈተኛ ቦታዎች በሰላም እየተካሔደ መሆኑን የትምህርትነት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG