በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይሮቢ ላይ ተጠለፉ ስለተባሉት የኦብነግ መሪዎች


An Indian laborer sleeps surrounded by mounds of mangoes at a fruit market in Hyderabad.
An Indian laborer sleeps surrounded by mounds of mangoes at a fruit market in Hyderabad.

የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባር አባላት ናቸው የተባሉ ሰዎችን ናይሮቢ ላይ ጠልፈዋል በሚል ተይዘው የነበሩ ሁለት የኬንያ ፖሊስ አባላት በዋስትና መለቀቃቸው ተዘግቧል፡፡




please wait

No media source currently available

0:00 0:05:55 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባር አባላት ናቸው የተባሉ ሰዎችን ናይሮቢ ላይ ጠልፈዋል በሚል ተይዘው የነበሩ ሁለት የኬንያ ፖሊስ አባላት በዋስትና መለቀቃቸው ተዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ሁለት የኦጋዴን ተወላጆች ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ መግባታቸውን አስታውቋል፡፡

ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ድርጅር ለማድረግ ናይሮቢ ገብተው የነበር የተባሉ ሁለት የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባር አመራር አባላትን በመጥለፍ የተጠረጠሩት ሁለት የኬንያ ፖሊስ አባላት የተለቀቁት በሁለት ሚሊየን የኬንያ ሽልንግ ወይም 427 ሺህ 840 የኢትዮጵያ ብር ዋስትና መሆኑን ዴይሊ ኔሽን የሚባለው የሃገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

የኬንያ ፖሊስ አባላት የሆኑት አንድ ኮንስታብል እና አንድ ኢንስፔክተር በቁጥጥር ሥር የዋሉት የዛሬ ሣምንት ጥር 22/2006 ዓ.ም እንደነበረ ሌላው የኬንያ ጋዜጣ ዘ ስታንዳርድ ዘግቦ ነበር፡፡

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር ከፍተኛ አመራር አባላት መሆናቸው የተነገረው ሱሉብ አሕመድ እና አሊ ሁሴን ናይሮቢ ውስጥ አራቢያን ክዊዚን ከሚባለው ምግብ ቤት ደጃፍ የተጠለፉት ባለፈው ዕሁድ፣ ጥር 18/2006 ዓ.ም ሲሆን ሰዎቹ ምናልባት በሞያሌ በኩል ለኢትዮጵያ ተላልፈው ተሰጥተው ሊሆን ይችላል ከሚል ግምት በስተቀር የት እንደሚገኙ በትክክል እንደማይታወቅ ሁለቱ የኬንያ ጋዜጦች አመልክተዋል፡፡

ለቪኦኤ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ግን ሰሞኑን ሁለት የኦጋዴን ተወላጆች ወደ ኢትዮጵያ በራሣቸው ፍላጎት በሰላም መግባታቸውን ገልፀው የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት በጉዳዩ ላይ በቅርቡ መግለጫ እንደሚሰጥ አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG