ምያንማር በዋና ዲፕሎማቷ ምትክ ፖለቲከኛ ያልሆነ ተወካይ እንድትልክ የቀረበላትን ግብዣ ውድቅ በማድረግ፣ በያዝነው ሳምንት በካምቦዲያ በሚካሄደው የደቡብ ምሥራቅ እስያ አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ አልሳተፍም አለች።
የማያንማርን ተሳትፎ ለመገደብ የሰጠው ውሳኔ ጦር ሰራዊቱ ስልጣን በኃይል ከተቆጣጠረ በኋላ ምያንማር የገጠማትን ከፍተኛ የፖለቲካ ቀውስ ለማርገብ 10 አባላት ያሉት ቡድን የተስማባቸውን እርምጃዎች ለመተግበር አልተባበር ማለቱን ተከትሎ የተደረሰ ነው።።
የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትናንት ሰኞ ቶኪዮ ላይ ከካምቦዲያው የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር እና ወታደራዊ አዛዥ ሁን ሰን ልጅ ጋር ተገናኝተው በምያንማር ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ ተባብረው በሚሰሩበት መንገድ ዙሪያ ተስማምተዋል። ካምቦዲያ የወቅቱ የደቡብ እስያ አገሮች ማኅበር ሊቀመንበር ነች።