ዋሺንግተን ዲ.ሲ. —
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዐርብ፤ ሚያዝያ 4/2005 ዓ.ም በተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሠልፎችን አካሂደዋል፡፡
በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድ ባለፈው ሣምንትና ዛሬም የወጣው ሰው በጣም ብዙ እንደነበረ አንድ የሠልፉ ተሣታፊ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
አንዋር መስጊድ ላይ ዱኣ ማድረጋቸውንና ሠልፈኛው “ፍትሕ” የሚል ፅሁፍ ይዞ እንደነበር፣ ነጭ ወረቀቶችን ሲያውለበልቡ እንደነበር ተገልጿል፡፡
“ሙስሊሞች ሠላም ለማደፍረስ ሳይሆን ድምፃችንን ለማሰማት፣ ፍትሕ ካለ የፍትሕ አካል እንዲሰማን ብለን ነው የወጣነው፤ የሰው ልጅ መብት መከበር አለበት፤ ኢትዮጵያ የሁላችንም ሃገር እስከሆነች ድረስ ፍትሕ መስፈን አለበት ብለዋል፡፡” እኒሁ ቪኦኤ ያነጋገራቸው ተሠላፊ፡፡
በሻሸመኔ ከተማ የተካሄደውን ሠልፍ አስመልክቶ የተናገሩ አንድ የከተማው ነዋሪ ደግሞ የወጣው ሰው ብዙ መሆኑንና ጥያቄዎቻቸውም ከቀደመው የተለየ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡
“ላቀረብነው ጥያቄ መንግሥት እስከአሁን ምላሽ ስላልሰጠን፣ ምላሽ እየጠበቅን መሆኑን ለመንግሥት ለማስገንዘብ ነው የወጣነው” ብለው ጥያቄዎቻቸውንም ደግመው ዘርዝረዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የሰሎሞን ክፍሌ ዘገባ ያዳምጡ፡፡