No media source currently available
ዐቃቤ ህግ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል ወንጀል በተከሰሱት አራት ተጠርጣሪዎች ለሁለት ተከታታይ ቀናት ምስክሮችን አሰምቷል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የህገ መንግሥትና የጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የዐቃቤ ህግ ምስክሮችን ሁሉ አዳምጦ መጨረሱም ተመልክቷል። የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ቤተሰቦችም በችሎቱ ላይ መገኘታቸውን ተገልጿል።