በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞዛምቢክ በሃገሩዋ ስለሚሰማሩ ጋዜጠኞች


የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ፊሊፕ ንዩሲ
የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ፊሊፕ ንዩሲ

ሞዛምቢክ በሃገሩዋ የሚሰማሩ ጋዜጠኞችን ከነገ ረቡዕ ጀምሮ በዓለም ወደር የሌለው የምዝገባ ክፍያ ማስከፈል ትጀምራለች።

ሞዛምቢክ በሃገሩዋ የሚሰማሩ ጋዜጠኞችን ከነገ ረቡዕ ጀምሮ በዓለም ወደር የሌለው የምዝገባ ክፍያ ማስከፈል ትጀምራለች።

አዲሱ የምዝገባ ክፍያ በስፋት የተነቀፈ ሲሆን ሂዩማን ራይትስ ዋች “ከልክ ያለፈ” ሲለው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከዚያች ሃገር መዘገብ የሚችል ላይኖር ነው ብሏል።

ለመሆኑ ሞዛምቢክ ምን ያህል ነው የምትጠይቀው? ሃገሩዋ ተቀምጦ የሚዘግብ ጋዜጠኛ በዓመት ስምንት ሽሕ ሦስት መቶ ዶላር አዲስ ራዲዮ ጣቢያ ለመክፈት ደግሞ ሰላሳ አምስት ሺህ ዶላር ይጠይቃል።

ለውጭ መገናኛ ብዙሃን የሚዘግብ የሀገር ውስጥ ጋዜጠኛ ለሥራ ፈቃዱ በዓመት ሦስት ሺህ አምስት መቶ ዶላር መክፈል ይኖርበታል። የሀገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት የነፍስ ወከፍ ገቢ በዓመት 1200 ዶላር መሆኑን ያስተውሏል።

የድንበር የሌሽ ጋዜጠኞች የአፍሪካ ክፍል ኃላፊ አርኖድ ፍሮዤይ የሞዛምቢክ መንግሥት የአከባቢ ምርጫዎች አንድ ወር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ደግሞ አንድ ዓመት ሲቀረው ይህን ማድረጉ በምርጫዎቹ ዙሪያ ዘገባዎችን ለማፈን ነው ሲሉ አውግዘዋል።

የሞዛምቢክ መንግሥት በበኩሉ አንድም ከምጣኔ ኃብት አኳያ ደግሞም ሚዲያውን ሥርዓት ለማስያዝ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል ባይ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG