ዋሺንግተን ዲ.ሲ.- ሞስኮ —
ሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ ላይ እየተካሄደ ባለው 14ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ አትሌቶች ያገኙት ድል በዓለሙ ሠንጠረዥ ሁለተኛ ቦታ ላይ አስቀምጧቸዋል፡፡
ጥሩነሽ ዲባባ በአሥር ሺህ ሜትር አንደኛ፣ በላይነሽ ኦልጅራ ሦስተኛ ሆነው ለኢትዮጵያ የወርቅና የነኀስ ሜዳልያዎችን ሲያስገኙ ደጀኔ ገብረመስቀል በወንዶች አሥር ሺህ ሜትር ሁለተኛ ሆኖ የብር ሜዳልያ አግኝቷል፡፡
ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በተካሄድ ውድድሮች ዩናይትድ ስቴትስ በሁለት ወርቅ አንድ ብርና አንዳ ነኀስ ሜዳልያዎች አንደኛ፣ ኢትዮጵያና ኬንያ አንድ ወርቅ አንድ ብርና አንድ ነኀስ እያንዳንዳቸው ይዘው ሁለተኛ ሆነው የዓለሙን የደረጃ ሠንጠረዥ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ቦታ እየመሩ ነው፡፡
የሞስኮ አትሌቲክስ ውድድሮች እስከፊታችን ዕሁድ ይቀጥላሉ፡፡

ለተጨማሪ ዝርዝር የዓለም አቀፎቹን የስፖርት ማኅበራት አማካሪ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔን እማኝነት የያዘውን የሰሎሞን ክፍሌን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡