ካይሮ —
የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሞርሲ ከሥልጣናቸው እንደማይነቃነቁ በቁርጠኝነት አስታወቁ፡፡
ፕሬዚዳንቱ ፍንክች እንደማይሉ አቋማቸውን ዛሬ - ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ምሽት ላይ ባደረጉትና በሃገሪቱ ብሔራዊ ራዲዮና በቴሌቪዥን በቀጥታ በተላለፈ ንግግር ያስታወቁት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚዎቻቸው አደባባይ ወጥተው እንዲወርዱ እየጠየቋቸው ባሉበት ወቅት ነው፡፡
የዛሬ ዓመት አካባቢ በሃገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደ ነፃ ምርጫ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ መሆናቸውን ያስታወሱት ፕሬዚዳንት ሞርሲ ሕገመንግሥታዊ ኃላፊነቶቻቸውን በመወጣት እንደሚቀጥሉ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡
የሃገሪቱ ጦር እጁን ከፖለቲካው ቀውስ ውስጥ እንዲያወጣም አሣስበዋል ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ንግግራቸው፡፡
በሚስተር ሞርሲ እና በተቃዋሚዎቻቸው መካከል ያለው ልዩነት እስከነገ፤ ረቡዕ ባለው ጊዜ ካልተፈታ ለግብፅ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ይበጃል የሚሉትን የራሣቸውን የጎዳና ትልም እንደሚደነግጉ የጦር ኃይሎቹ መሪዎች ማስጠንቀቃቸውና ቀነ-ገደብ መቁረጣቸው ይታወሣል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ንግግራቸውን እያሰሙ በነበሩበት ወቅት ቁጥራቸው የበዛ ተቃዋሚና ደጋፊዎቻቸው የሆኑ ሰልፈኞች የካይሮን አደባባዮችና ጎዳናዎች አጨናንቀዋል፡፡
ከመሪያቸው ጎን ቆመው እነርሱ “ማንኛውም ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት” ያሉትን የጦሩን እርምጃ በቁርጠኝነት እንደሚፋለሙ እየዛቱ ያሉት የሞርሲ ደጋፊዎች በዋና ከተማይቱ ናስር ቀበሌ የተሰባሰቡ ሲሆን ሞርሲ ሥልጣናቸውን መልቀቅ አለባቸው የሚለውን ጥያቄአቸውን የሚያሰሙት ተቃዋሚዎች ደግሞ ማዕከላዊውን የካይሮ ጣሕሪር አደባባይ ሞልተውታል፡፡
በሁለቱ ወገኖች መካከል በተነሣ ግጭት ካይሮ ውስጥ ዛሬ (ማክሰኞ) የሰባት ሰው ሕይወት መጥፋቱን የሕክምና ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ወታደሮቹ “ሕገመንግሥቱን ለማቋረጥ፣ ሕግ አውጭውን አካል ለመበተንና የሽግግር አስተዳደር ለማቋቋም እየተዘጋጁ ነው” የሚል ሾልኮ የወጣና ለመንግሥቱ የዜና አገልግሎት ሽው ያለ ጭምጭምታ ጠቁሟል፡፡
የፕሬዚዳንቱ ሙስሊም ወንድማማችነት ፓርቲ አባላት “የተመረጠን ፕሬዚዳንት ለመገልበጥ የሚደረግን ሙከራ ለማቆም” ከታንኮች ፊት ቆመው መስዋዕት እንደሚከፍሉ እየዛቱ ነው፡፡
ፕሬዚዳንት ሞርሲ ተቃዋሚዎቹን ሰልፈኞች እያዳመጡ መሆናቸውን እንዲያሣዩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ማክሰኞ ጠዋት ስልክ ደውለው ጠይቀው ተቃዋሚዎችም የግብፅን ዴሞክራሲያዊ ሂደት መንገድ እንዲከተሉ አሳስበዋል፡፡
አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሔ እንዲሹ ለግብፃዊያኑ ጥሪ አሰምተዋል፡፡
ባለፉት ሁለት ሣምንታት ውስጥ በተካሄዱ ሰልፎችና በተነሱ ግጭቶች ሳቢያ ከሃያ በላይ ሕይወት መጥፋቱ ተዘግቧል፡፡