በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለምአቀፍ የፍልሰት ሰነድ በአንድ መቶ ሃምሣ ሃገሮች ፀደቀ


ሞሮኮዪቱ ከተማ ማራኬሽ ውስጥ ዛሬ በተከፈተ የሁለት ቀናት ጉባዔ ላይ የተናገሩት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ “የፍልሰት ጉዳይ መመራት በአግባቡና ደኅንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንጂ በዘፈቀደና አደገኛ በሆነ መንገድ አይደለም” ብለዋል።

ሞሮኮዪቱ ከተማ ማራኬሽ ውስጥ ዛሬ በተከፈተ የሁለት ቀናት ጉባዔ ላይ የተናገሩት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ “የፍልሰት ጉዳይ መመራት በአግባቡና ደኅንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንጂ በዘፈቀደና አደገኛ በሆነ መንገድ አይደለም” ብለዋል።

ለዓለምአቀፉ ሥርዓትን የጠበቀና ያልተዛባ የፍልሰት ሂደት ቁልፍ ናቸው ያሏቸውን አብዛኞቹ አውሮፓዊያን የሆኑ ሃገሮችን ዋና ፀሐፊው በአድናቆት አንስተዋል።

ሰነዱ በሃገሮች ላይ ‘የፍልሰት ፖሊሲዎችን በመጫን ሉዓላዊነታቸውን ሊዳፈር ይችላል፤’ ሰዎች ‘ወደፈለጉበት ቦታ ሁሉ ባሻቸው ጊዜ መንቀሳቀስ እንችላለን’ ብለው እንዲያስቡ የሚያደርግ ‘መብት ፈጥሮ ዕውቅና ይሰጠዋል’ የሚል ሥጋት ያላቸው ሁሉ “ተሳስተዋል” ብለዋል ጉቴሬዥ።

ይህ የፍልሰት ሰነድ የሚያደርገው ብቸኛ ቁምነገር “የሰዎች የፍልሰት ሁኔታ ግምት ውስጥ ሳይገባ ሰብዓዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው በድጋሚ ማረጋገጥ ብቻ ነው” ብለዋል አክለው።

ይህ የሕግ አስገዳጅነት የሌለው ዓለምአቀፍ የፍልሰት ሰነድ መሠረታዊ አገልግሎቶችን የማግኘት ዕድልን ማስፋትን፣ ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር ማስሾለክና ከቦታ ቦታ ማዘዋወርን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ጥረቶችን ማጠናከርን፣ ጅምላ መድልዎና ማግለልን ሙሉ በሙሉ ማስወገድን፣ ሰዎች የሚሠሩት ሥራ የተከበረ መሆኑን የሚያረጋግጥላቸው የሥራ ሁኔታ እንዲጠበቅ ማድረግ፣ ወደ ትውልድ ሃገሮቻቸውና የቀድሞ አካባቢዎቻቸው መመለስ የሚፈልጉ ሰዎች ደኅንነቱ የተጠበቀና ክብር ያለው ጉዞና መድረሻ እንዲኖራቸው ማድረግን ጨምሮ ሃያ ሦስት ዓላማዎች ያሉት ነው።

ሰነዱ ከኢሚግሬሽንና የስደተኞች ጉዳዮች ፖሊሲዎቿ ጋር ይጋጫል በሚል ባለፈው ዓመት ታኅሣስ ከስምምነት ሃሣቡ እራሷን አስወጥታለች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG