ዋሺንግተን ዲሲ —
በምስራቅ ሶሪያ ሩስያ ያወጀችው ተኩስ አቁም በሚመለከታቸው በሽምቅ ተዋጊ ይዞታ ባሉት የምሥራቅ ሶሪያ ጉታ አካባቢዎች ውጊያው መቀጠሉን የሚገልጹ ሪፖርቶች ደርሰውናል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።
በየቀኑ ለተወሰነ ጊዜ ተኩስ እንዲቋረጥ የታወጀው ሲቪሎች ከውጊያው አካባቢ ለመውጣት እንዲችሉ ተብሎ መሆኑ ተገልጿል።
የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ ቃል አቀባይ ዬንስ ላርከ በአካባቢው አሁን ያለው ሁኔታ ኮንቮዮች የሚገቡበት ወይም ለህክምና ርዳታ ሲቪሎችን ማውጣት የሚቻልበት አለመሆኑ ግልፅ ነው ብለዋል።
ሩስያና ሶሪያ ሲቪሎች የሚወጡበትን መሥመርና ደማስቆ አካባቢ ድብደባ ያካሄዱት ተቃዋሚ ታጣቂዎች ናቸው ብለው ወንጅለዋል ተቃዋሚዎች ግን አስተባብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ