የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የኣባታቸው የትውልድ ሃገር የሆነችውን ኬንያን እና በመቀጠልም ኢትዮጳያን ይጎበኛሉ ። ፕሬዚደንቱ ነገ ኣርብ ኬንያ የሚገቡ ሲሆን በእለቱ ዋና ከተማዋ ናይሮቢ በሚካሄደው ኣለም ኣቀፍ የንግድ ፈጠራ ጉባኤ Global Entrepreunership Summit ላይ ይካፈላሉ።
የኦትዮጳያ ጉብኝታቸው ጥያቄዎችን ኣስነስቱዋል ኢትዮጳያ በምጣኔ ሃብት ረገድ ከፍተኛ ስኬቶችን ያስመዘገበች ,,, እያደገች ያለች ሀገር መሆንዋ እንዳለ ሆኖ ,,, ከባድ ችግሮች ኣሉባት። በፕሬሱ ላይ ከባድ የሆነ ኣፈና ይካሄዳል።በዚህ ሁኔታ ፕሬዚደንት ኦባማ የሚያደርጉት ጉብኝት የተሳሳተ መልእክት ያስተላፋል የሚሉ ነቃዋፊዎች ተብለው የተጠየቁት ዋሽንግተን የሚገኘው የWoodrow Wilson ማእከል የኣፍሪካ ፕሮግራም ድሬክተር Monde Muyangwa
የኣፍሪካን ጉዳይ ኣትኩሮ ከሚከታትለው ማህበረሰብ ውስጥ በኣንዳንዶች ዘንድ ሁለቱንም ኬንያና ኢትዮጳያን ለፕሬዚደንቱ ጉብኝት መመረጣቸው ውዝግብ ያስነሳ ይመስለኛል።ሁለቱንም ሃገሮች ኣስመልክቶ የውዝግቡ መንስኤ የሆነው ቁልፉ ጉዳይ የኣስተዳደር እና የሰባዊ መብት ጉዳይ ነው ካሉ በሁዋላ ነገር ግን ኬንያና ኢትዮጳያ በተለይ ጸጥታን በሚመለከቱ ጉዳዮች የዩናይትድ ስቴትስ ቁልፍ ኣጋሮች መሆናቸውን ማስታወስ እንደሚገባ ኣሳስበዋል
ሁለቱም ሃገሮች በሶማሊያ ባለው ሁኔታ ከባድ የጸጥታ ፈተና የተደቀነባቸው ሃገሮች ናቸው። ይህ የጸጥታ ችግር ደግሞ የነሱ ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ የኣፍሪካ ቀንድ ላይ የተደቀነ ኣልፎም ኣለም ኣቀፍ ስጋት ነው። በዚህ ረገድ ሁለቱም ሃገሮች የዩናይትድ ስቴትስ ሸሪኮች ናቸው ። ፕሬዚደንቱ የሚያደርጉት ጉብኝት ሁለቱ ሃገሮች በክልሉ ሰላምና ጸጥታን ለማስፈን እና ኣልሸባብን በሶማሊያና ባጠቃላይ በክልሉ ለመታገል ስለሚያበረክቱት ኣስተዋጽኦ በግንባር ተገኘተው ለማመስገን እድል ይፈጥርላቸዋል ።ሁለቱ ሃገሮች በተባባሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልእኮ ውስጥ ስለሚጫወቱት ሚናም እንዲሁ።
ኣስተዳደርን እና ሰብኣዊ መብቶችን በተመለከተ የሚሰሙት ስጋቶችም ተገቢ ስጋቶች ናቸው።
ፕሬዚደንቱ በሁለቱም ሃገሮች በሚያደርጉዋቸው ጉብኝቶች ጉዳዩን እንዲያነሱ ማበረታታት ያስፈልገናል። እንደሚያነሱም እርግጠኛ ነኝ ። እነዚህን ጉዳዮች ለማንሳት ኣመቺ እድል ማግኘት ወሳኝነት ኣለው። ምክንያቱም ዩናይትድ ስቴትስ መርሆችዋን ተመርኩዛ በተኣማኒነት ድምጹዋን ማሰማት የምትችልባቸው ጉዳዮች ስለሆኑ ። ኣፍሪካዊያንም እንደህዝብ ከዩናይትድ ስቴትስ ይህን ይጠብቃሉ ብለዋል። የኢትዮጳያ ጉዞኣቸው በኣፍሪካ ህብረት መድረክ ተጠቅመው ለኣጠቃላዩ የኣፍሪካ ህዝብ በነዚህ ቁልፍ ጉዳዮች ዙሪያ የሚናገሩበት እድል ተደርጎ መታየት ኣለበት ብለዋል።