በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አልሸባብ በሞቃድሾ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ጥቃት አደረሰ


አልሸባብ በሶማልያ በከፍተኛ ጥበቃ ስር በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ጥቃት መፈጸሙን የሶማልያ ፖሊስ ቃል አቀባይ አስታወቁ፡፡

ቃል አቀባዩ ለቪኦኤ የሶማልኛ ክፍል ጨምረው እንዳስታወቁት አጥቂዎቹ የተጋፈጧቸውን ሁለት የጸጥታ ሰራተኞች መግደላቸውንና ሶስት የፖሊስ አባላት መቁሰላቸውን ተናግረዋል፡፡

የአልሸባብ ኃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን በጥብቅ ጥበቃ ስር የነበረውን ተቋም ጥሶ መግባቱና አስታውቋል፡፡ አውሮፕላን ማረፊያው በሶማልያ የአፍሪካ ህብረት ተልእኮን ጨምሮ በሞቃዲሾ የሚገኙ በርካታ የውጭ ዲፕፕሎማቶች ያሉበት አካባቢ መሆኑን ተነግሯል፡፡

በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞችና የጸጥታ ባለሥልጣናት ለቪኦኤ የሶማልኛው ክፍል እንደተናገሩት ጥቃቱ የተፈጸመው በአውሮፕላን ማረፈፊያው በስተስሜን አቅጣጫ ለአየር ኃይሉ የጦር ስፈር ቅርብ በሆነ ስፍራ ነው፡፡

XS
SM
MD
LG