በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞደርና "ክትባቱ ለህጻናት ቢሰጥ ውጤታማ ነው" አለ


በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው የኮቪድ-19 ክትባት መድሃኒት አምራች ሞደርና፣ በሰዎች ላይ የተደረጉ የሙከራ ውጤቶች አነስተኛ መጠን ያላቸው የኮቪድ -19 ክትባቶች እድሜያቸው ከ6 እስከ 11 ለሚደርሱ ህጻናት ቢሰጥ አስተማማኝ ውጤት ያሳያል አለ፡፡

ድርጅቱ ይህን ያለው 4ሺ700 ለሚደርሱ ህጻናት በ28 ቀናት ልዩነት ውስጥ፣ ለአዋቂዎች ከሚሰጠው ግማሽ ያህሉን ሁሉቱንም የሞደርና ክትባቶች በመስጠት ባደረገው ሙከራ ነው፡፡

የሙከራው የመጀመሪያ ውጤት፣ በህጻናት ውስጥ ያለው የተፈጥሮ የመከላከል አቅም ሙሉውን ክትባት የወሰዱት አዋቂዎች ካላቸው አቅም ጋር ተመሳሳይ ሆኖ መገኘቱንም ሞደርና አስታውቋል፡፡

ክትባቱን የሚወስዱ ህጻናት ክትባቱ በተሰጣቸው ስፍራ ላይ እንዳሉ መጠነኛ የድካም፣ ራስ ምታትና ትኩሳት የመሳሰሉት ህመሞች ሊሰሟቸው እንደሚችሉም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG