በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት 3.2 ቢሊዮን ብር የሚገመት የውሀ መሰረተልማት መውደሙን የውሀ እና ኤነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ገለፁ፡፡
ከትግራይ እና ከአማራ ክልሎች ያነጋገርናቸው ነዋሪዎችም የውሀ ተቋማቱ በጦርነቱ በመውደማቸው ችግር መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ተቋማቱን ለመጠገን የአጭር እና የረዥም ጊዜ ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ መሆኑን ዶ/ር ሀብታሙ ገልፀዋል፡፡
አስተዳደራዊ መዋቅር ባለባቸው የአፋርና የአማራ ክልሎች ከውሀ ቢሮዎች ጋራ እየተሠራ እንደሆነ የተናገሩት ዶ/ር ሀብታሙ፣ በትግራይ ክልል ግን መዋቅሩ ስለሌለ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከማዕከል ባለሞያዎችን እየላከ የጥገና ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ያገኛሉ።