በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመለስ ፈገግታ አይረሣኝም - አኒታ ፓወል


ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ብዙ ሲያነጋግር ከቆየው የጤናቸው ሁኔታ በኋላ በሕመም ምክንያት በሃምሣ ሰባት ዓመት ዕድሜአቸው ማረፋቸው ተነገረ፡፡

ባለፈው ማክሰኞ በመንግሥቱ የቴሌቨዥን ጣቢያ በተሰማው መርዶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውጭ ሃገር በሕክምና ላይ ሣሉ በገጠማቸው ድንገተኛ ኢንፌክሽን ሣቢያ ሰኞ - በቀደመው ዕለት ማለት ነው - ሕይወታቸው ማለፉ ተነገረ፡፡

ጆሃንስበርግ የምትገኘው የቪኦኤ ዘጋቢ አኒታ ፓወል ላለፉት ሁለት ዓመታት የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ወጣ ገባ እየተከታተለች ስትዘግብ ቆይታለች፡፡ የማስታወሻ ደብተሮቿን ገለጥ ገለጥ አደረገችና የሚከተለውን ትውስታዋን ፃፈች፡፡

ስለኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፈፅሞ የማልረሣው ነገር ሰፊው ፈገግታቸው ነው፡፡ ሙሉ ፊታቸው ነበር የሚስቀው፡፡ ዐይኖቻቸው ይርገበገባሉ፤ እራሣቸው ወደፊት ይታጠፋሉ፤ ደስታቸውን፤ ፍንደቃቸውን ለሰዉ ለማካፈል የሚፈልጉ ነበር የሚመስለው፡፡

ተፈታታኝ ጥያቄዎችን ባቀረብኩላቸው ቁጥር ያንን ፈገግታቸውን ነበር የሚሰጡኝ፡፡
….
መለስ እራሣቸው በራሣቸው መንገድ ትክክል ነው ባሉት የሥነ-ልቦና ተክል ያመኑና በዚያው የገፉ ሰው ነበሩ - ነቃፊዎቻቸው ያንን “ዕብሪት” ብለው ይጠሩታል፤ ምናልባት ትክክል ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
….

ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:25 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG