በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተቃዋሚዎች መነጋገር ይፈልጋሉ


Picha ya kampeni ya Rais Meles Zenawi wa Ethiopia
Picha ya kampeni ya Rais Meles Zenawi wa Ethiopia
የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሕልፈት ተከትሎ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች መግለጫዎች እየወጡ ነው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መንግሥት ሽብርተኞችና ከሃዲዎች እያለ የሚጠራቸው ሁለት ተቃዋሚ ድርጅቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕልፈት በኋላም የሚፈልጉት ከመንግሥቱ ጋር ወመያየት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በየድርጅቶቻቸው ስም መግለጫዎቻቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ያሳወቁት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ወንድምአገኘሁ ደነቀ፣ የአረና ትግራይ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አሥራት እና የኦሮሞ የምክክር መድረክ የውጭ ጉዳይ ተጠያቂና ቃልአቀባይ አቶ ሌንጮ ባቲ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ከመለስ ጋር የግል ፀብም ሆነ ቂም እንደሌላቸው ያመለከቱትና ክፉም እንደማይመኙላቸው የጠቆሙት የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ልዩነቶችን በሰፋ ሁኔታ ማስተናገድ የሚችልና ክፍት መድረክ ያለው መንግሥት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

የታጠቀው ቡድናቸው የራስን ዕድል በራስ ለመወሰን መሣሪያ አንስቶ እየተዋጋ ያለ ከመሆኑ በስተቀር በሲቪሎች ላይ የሚያደርሰውም ሆነ የሚቀሰቅሰው ጥቃትና የአመፃ ተግባር የሌለ በመሆኑ በኢትዮጵያ መንግሥት ሽብርተኛ ተብሎ መጠራቱ አግባብና ትክክል አለመሆኑን የሚናገረው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ቃል አቀባይ አብዱልራህማን ማህዲ ግንባራቸው ያገኛቸው አማፂ ቡድኖች ሁሉ የሚስማሙበት አንድ ነጥብ ወደፊት ለመራመድ መነጋገር አስፈላጊ የመሆኑ ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ቅርፅ ላይ የሚለወጥ አንዳች ነገር እንደማይኖርና ሁሉም ነገር በነበረው ሁኔታ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ሽመልስ ከማል ተናግረዋል፡፡


please wait

No media source currently available

0:00 0:11:56 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG