በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ክልል የርዳታ እህልን በሚሸጡ ግለሰቦች ላይ ርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ


የትግራይ ክልል የርዳታ እህልን በሚሸጡ ግለሰቦች ላይ ርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:36 0:00

በትግራይ ክልል፣ በገበያ ላይ ከሚታዩት የርዳታ እህሎች ውስጥ፣ የሕፃናት አልሚ ምግቦች በብዛት እንደሚገኙበት፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ዳይሬክተር ገለጹ፡፡

በትግራይ ክልል ጉብኝት ያደረጉት፣ በኢትዮጵያ የተቋሙ ዳይሬክተር ክላውድ ጂቢዳር፣ በጉዳዩ ላይ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋራ የተወያዩ ሲኾን፣ በመቐለ ከተማ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው፣ ለርዳታ ፈላጊዎች የሚለገሰውን ምግብ በመሸጥ ጽዩፍ ተግባር ላይ የተሠማሩ ግለሰቦችን ለማስተካከል ርምጃ እንደሚወሰድ በቲዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

በዚኽ ዙሪያ የተሰናዳውን ሙሉ ዘገባ ለማድመጥ የተያያዘውን ፋይል ይጫኑ።

XS
SM
MD
LG