ከራያ አላማጣ ወረዳ እና የአላማጣ ከተማ ተፈናቅለው በመኾኒ፣ በማይጨው እና በመቐለ ከተማ ተጠልለው የቆዩ ከ17 ሺሕ በላይ ነዋሪዎች ወደ ቀዬአቸው መመለሳቸውን ያስታወቀው የትግራይ ደቡባዊ ዞን አስተዳዳር፣ የመጨረሻዎቹ ተመላሾች በዛሬው ዕለት መግባታቸውን ገልጿል።
የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ሃፍቱ ኪሮስ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ ከአሁን በኋላ ተፈናቃዮችን መልሶ የማቋቋሙ ሒደት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተናግረዋል።
ላለፉት 21 ወራት ከቤተሰቦቻቸው ተለያይተው በችግር ውስጥ እንደነበሩ ያስታወሱት ተፈናቃዮችም፣ ወደ ቀዬአቸው መመለሳቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።