በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አበላቸው ያልተከፈላቸው የመቐለ ከተማ ጡረተኞች “በሥቃይ ውስጥ ነን” አሉ


አበላቸው ያልተከፈላቸው የመቐለ ከተማ ጡረተኞች “በሥቃይ ውስጥ ነን” አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:50 0:00

“ለሁለት ዓመት የጡረታ አበል ክፍያ ተከልክለናል፤” ያሉ፣ የመቐለ ከተማ ነዋሪ ጡረተኞች፣ ሰልፍ አካሔዱ፡፡

የጡረታ አበል ክፍያው፣ አገራቸውን በማገልገል ሠርተው እና ደክመው ያጠራቀሙት እንደኾነ የገለጹት የከተማው ጡረተኞች፣ ለሁለት ዓመት ሳይከፈላቸው በመቆየቱ፣ በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ “ለአገር ያገለገልን ባለውለታዎች ኹነን መሸለም ሲገባን፣ ሥቃይ ውስጥ እንገኛለን፤ በረኀብ እና በሕመም ሕይወታቸው የሚያልፍ ጡረተኞች ቁጥር እየጨመረ ነው፤” ሲሉ አቤቱታ አሰምተዋል፡፡

በተመሳሳይ፣ 600 የሚኾኑ የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ቋሚ ሠራተኞች፣ ላለፉት ሁለት ዓመታት ደመወዝ ስላልተከፈላቸው፣ በችግር ውስጥ እንደሚገኙ፣ ምክትል ሥራ አስኪያጁ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ጡረተኞቹ በሰልፍ ላቀረቡት የጡረታ አበል ክፍያ እና ለስኳር ልማት ፕሮጀክቱ ቋሚ ሠራተኞች የደመወዝ ጥያቄ፣ ምላሽ ለማግኘት፥ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የሰላም ስምምነቱን በጠበቀ መልኩ፣ ከፌዴራሉ መንግሥት ጋራ እየተነጋገረበት እንደኾነ፣ የጽሕፈት ቤቱ ሓላፊ አቶ ዐማኑኤል አሰፋ ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG