በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመቀሌው የአንድነት ሰልፍ ተሠረዘ


አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ
አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ

አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ከትናንት በስተያ ዕሁድ በመቀሌ ከተማ እንዲካሄድ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ መሠረዙ ታወቀ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:51 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ከትናንት በስተያ ዕሁድ በመቀሌ ከተማ እንዲካሄድ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ መሠረዙ ታወቀ።

ለሠልፉ መሠረዝ በፓርቲው አመራር የተሰጠው ምክንያት የከተማዋ ባለሥልጣናት ሰልፉ እንዲካሄድ ስላልፈቀዱና ሕዝቡን መቀስቀስ እንዳይችሉም በፖሊስ ትዕዛዝ እንደተከለከሉ የሚጠቁም ነው።

የፓርቲው የሕግና የሰብዓዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ኃላፊ አቶ ደምሴ መንግሥቱ እንደገለፁት የአመራር አባሎቻቸውም ታሥረዋል።

ፖሊስ በበኩሉ የተቃውሞ ሰልፉ እንዳይካሄድ አልከለከልንም፤ ነገር ግን መቀሌ ከተማ ውስጥ በድምፅ ማጉያ እንዳይቀሰቅሱ ሕግን መሠረት በማድረግ ከልክለናል ብሏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የግርማይ ገብሩ ዘገባ ያድምጡ።
XS
SM
MD
LG