መቀሌ —
አቶ ገብረእግዚአብሔር ታደለ የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - ኢዴፓ የመቀሌ - ትግራይ ቅርንጫፍ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ናቸው።
ከዘጋቢአችን ግርማይ ገብሩ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በክልሉ ለሕዝብ የፓርቲአቸውን ፕሮግራም ለማስተዋወቅ ያደረጉት ጥረት አጥጋቢ እንዳልነበረ ገልፀዋል። ምክንያቱንም ሲያስረዱ በእርሣቸውና አባሎቻቸው ላይ ከመንግሥት ካድሬዎች ዛቻና ወከባ እንደደረሰ አስረድተዋል።
የተቃዋሚው ኢዴፓ አባል ሰለሆኑም በቤተሰባቸው ላይ ማግለልና ወከባ እንደሚደርስ ገልፀው ለምሳሌ የአባታቸው የእህት ልጅ ሲሞቱ በቀብሩ ሥነ-ሥርዓት ወቅት ባህሉ እንደሚፈቅደው አባታቸው የሚደግፋቸው እንዳጡ ገልፀዋል።
የመቀሌው የኢዴፓ መሪ ለግርማይ ገብሩ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ያድምጡ።