በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመድረክ ሰልፍ ለሃያ ቀናት ተለወጠ


የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ሕንፃ እና የመድረክ ዓርማ
የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ሕንፃ እና የመድረክ ዓርማplease wait

No media source currently available

0:00 0:02:00 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ትናንት ዕሁድ ፤ ኅብር 8 / 2006 ዓ.ም ሊያደርግ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ወደ ኅዳር 29 / 2006 ዓ.ም ለማዛወር መወሰኑን አስታውቋል፡፡

መድረክ ሰላማዊ ሰልፉን ትናንት የሠረዘው የከተማዋ የሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባዎች ዕውቅና ሰጭ አካል ለመድረክ በፃፈው ደብዳቤ በዕለቱ በከተማይቱ የተለያዩ ዓለምአቀፍ ስብሰባዎች እንደሚካሄዱ ገልፆ ለጥበቃ ይሠማሩ የነበሩ የፀጥታ ኃይሎች ዕጥረት ስላለ የግንባሩን ጥያቄ ማስተናገድ እንደማይችል በማስታወቁ መሆኑን የመድረክ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

በመጭ ቀናትም በከተማይቱ ውስጥ ተመሣሣይ ክንውኖች ስለሚደረጉ በዚህ ወቅት እንዲህ ዓይነት ጥያቄዎችን ማስናገድ እንደማይቻልም አስተዳደሩ መግለፁን ሊቀመንበሩ አመልክተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡
XS
SM
MD
LG