በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ውይይት ከመድረክ አመራር አባላት ጋር፣ የወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ


“አቶ መለስ ሕግ ነው፤ እርሱ ያለው ነገር ሕግ ሆኖ ይወጣል፡፡ አቶ መለስ ፍርድ ቤትም ነው፤... … አንድ ሰው እንደጎደለ ተደርጎ መታየት የለበትም” - አቶ ስዬ አብርሃ፡፡

“አቶ መለስ ሕግ ነው፤ እርሱ ያለው ነገር ሕግ ሆኖ ይወጣል፡፡ አቶ መለስ ፍርድ ቤትም ነው፤ በኢትዮጵያ ነፃ ፍርድ ቤት የሚባል ነገር የለም፤ እርሱ ያለው ፍርድ ሆኖ ይወጣል፡፡ ነፃ የዳኝነት ሥርዓት የለም፤ ነፃ የሕግ አውጭ የለም፤ የሕግ የበላይነት የለም፤ ሃሣብን በነፃነት የመግለፅ መብት ታፍኖ ቆይቷል፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው እንደጎደለ ተደርጎ መታየት የለበትም” ብለዋል አቶ ስዬ አብርሃ፡፡

“ኢትዮጵያ ከመለስ በኋላ ወደየት ታመራለች? የሠራዊቱ ስብጥር ምን ይመስላል? ሁኔታዎች የወታደሩን ጣልቃገብነት ሊጋብዙ ይችላሉ ወይ? የሚሉ ጥያቄዎችና የሃገሪቱን የኢኮኖሚ ጉዳዮችም በዚህ ውይይት ተነስተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተካፈሉት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ አመራር አባላት የሆኑት አቶ ገብሩ አሥራት፣ አቶ ተመስገን ዘውዴ እና አቶ ስዬ አብርሃ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ የተካሄደውን ውይይት ያስተናገደው ሰሎሞን ክፍሌ ነው፡፡ ድምፁ በዚህ ገፅ ላይ በሁለት ክፍሎች ሠፍሯል፤ ሙሉውን ያዳምጡ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:17:08 0:00
ቀጥተኛ መገናኛplease wait

No media source currently available

0:00 0:16:12 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG