በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመድረክ መግለጫና የአባይ ልማት


መድረክ ለአገራዊ መግባባት ጥሪ አቀረበ፡፡ ኢሕአዴግን በመከፋፈልና በማለያየት ወቀሰ፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በአባይ ወንዝ ላይ የሚሠራውን ግድብ በፅንሰ-ሃሣብ ደረጃ ቢቀበለውም አገራዊ መግባባት መቅደም አለበት ይላል፡፡

የስድስቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ በፅሁፍ ባሠራጨው መግለጫ "መድረክ መሠረታዊና የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሁኔታ ያገናዘበ ልማትን መቼም አይቃወምም፡፡" ብሏል፡፡

ይህንን መግለጫ ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ያብራሩት የመድረኩ የወቅቱ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አሥራት የአባይ ግንባታ በፀጥታም፣ በኢኮኖሚም፣ በልማትም፣ በዲፕሎማሲም ዳራው በጣም ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው የዜጎች ከማንኛውም ጊዜ በላይ መተባበር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡

"ኢሕአዴግ ግን - አሉ አቶ ገብሩ አሥራት አክለው - ሕዝቡን በማስተባበር ፋንታ እየለያየውና እየበታተነው ይገኛል፡፡"

አቶ ገብሩ በመቀጠል "አባይ ብቻ ሣይሆን በሃገሪቱ ሊሠሩ የሚችሉ ትላልቅ ነገሮች ሲኖሩ የምልዐተ-ሕዝቡ ትብብር፣ አንድ መሆን፣ በጋራ መቆም ያስፈልጋል" ብለዋል፡፡ "በኢሕአዴግም በኩል መሠረታዊ ለውጦች አስፈላጊ ናቸው" ሲሉ መክረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG