ዋሺንግተን ዲ.ሲ.- አዲስ አበባ —
ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላንና ኦሮሚያ ውስጥ ካለው ሁኔታ ጋር ተያይዞ መድረክና አጋር ድርጅቶቹ ለዕሁድ፤ ግንቦት 10/2006 ዓ.ም ጠርተውት የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ለመጭው ቅዳሜ ማዛወራቸውን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ፀሐፊና የመድረክ ሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ በቀለ ነጋ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በነጆ አካባቢ ደምቡ በሚባል ሥፍራ ለገበያ በወጣ ሰውና በፀጥታ መካከል ግጭት ተፈጥሮ በርካታ ሰው መታሠሩን አቶ በቀለ ጠቁመው በሌሎች የኦሮሚያ አካባቢዎች ሁኔታው ፀጥታ የሠፈነበት መሆኑን አመልክተዋል፡፡
የነጆን የዛሬ ሁኔታ ለጊዜው ከሌላ ወገን ማጣራት አልተቻለም፡፡
ከሠላማዊ ሠልፉ ዝግጅት ጋር ተያይዞ እስከአሁን በአባሎቻቸው ላይ የደረሰ ችግር አለመኖሩን አቶ በቀለ አክለው ገልፀዋል፡፡
ከአቶ በቀለ ነጋ ጋር ዛሬ ያደረግነውን አጭር ቃለምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡