በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞሪሺየስ በውቅያኖስ ማዕበሉ ምክንያት በረራዎች አቋረጠች


ሞሪሺየስ በውቅያኖስ ማዕበሉ ምክንያት ሞሪሺየስ በረራዎች አቋረጠች፡፡
ሞሪሺየስ በውቅያኖስ ማዕበሉ ምክንያት ሞሪሺየስ በረራዎች አቋረጠች፡፡

ሞሪሺየስ ከህንድ ውቅያኖስ የተነሳው “ፍሬዲ” የተባለው ከባድ ማዕበል እየተቃረበ በመሆኑ በረራዎች እንዳይነሱ ያደረገች ሲሆን የአክሲዮን ልውውጥ ገበያዋንም ዘግታለች፡፡

ማዳጋስካር ደግሞ በአራት ክፍል ግዛቶቿ የከባድ ዝናብ፣ የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ ይደርሳል በሚል ሥጋት የአጣዳፊ ዕርዳታ ሰራተኞች አዘጋጅታለች፡፡

በሰዓት 120 ኪሎ ሜትር ፍጥነት የሚነጉደው ማዕበል ሞሪሺየስ ላይ በቀጥታ አደጋ እንደደቀነ የሀገሪቱ አየር ሁናቴ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

ከሞሪሺየስ 1130 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በማዳጋስካር ደሴት ደግሞ ማዕበሉ ነገ ማክሰኞ ማታ ሁለት ክፍለ ግዛቶቿን እንደሚመታ ባለሥልጣናቱ ገልጸዋል፡፡

ካሁን ቀደምም ሁለቱ የህንድ ውቅያኖስ ደሴቶች እና ሞዛምቢክ በተደጋጋሚ በመታቸው የሰው ህይወት ባጠፋ ኃይለኛ ዝናብ እና ማዕበል በብዙ ሺዎች የተቆጠሩ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው፡ ህንጻዎች መፈራረሳቸውና ሰብል መውደሙ ይታወሳል፡፡

ባለፈው ጥር ወር በደረሰው ከባድ የውቅያኖስ ማዕበል እና ዝናብ ማዳጋካር ውስጥ 33 ሰዎች ሞተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG