በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለታሠሩ የሻማ ሥነ-ሥርዓት ዋይት ሃውስ ደጅ ላይ ተካሄደ


የሻማ ሥነ-ሥርዓት ዋይት ሃውስ ደጅ - ዕሁድ ታኅሣስ 21 / 2005 ምሽት
የሻማ ሥነ-ሥርዓት ዋይት ሃውስ ደጅ - ዕሁድ ታኅሣስ 21 / 2005 ምሽት

በዋሽንግተን ዲሲና አባባቢዋ ያሉ የተወሰኑ ትውልደ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ዕሁድ ታኅሣስ 21 / 2005 ምሽት ላይ ሻማ የማብራት ሥነ-ሥርዓት አካሂደዋል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:00 0:00
ቀጥተኛ መገናኛበአዲሱ የአውሮፓዊያን ዓመት መባቻ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ለኢትዮጵያ ጉዳዮች ትኩረት እንዲሰጡ ለማሳሰብና ኢትዮጵያ ውስጥ ያለአግባብ ታስረዋል ያሏቸው የፖለቲካ እሥረኞች እንዲፈቱ በመጠየቅ ነው የሻማው ዝግጅት የተካሄደው፡፡

ሥነ-ሥርዓቱ የተከናወነው በዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ፊት ለፊት ሲሆን ጠሪው ማርች ፎር ፍሪደም የሚባለው ድርጅት ነው፡፡

ድርጅቱ ቀደም ሲል በበተነው ጥሪ “ወገኖቻችን በሰላማዊ መንገድ ለነፃነት፣ ለፍትሕ፣ ለሰው ልጅ እኩልነትና ለሰብዓዊ መብቶች፣ ለእምነት ነፃነት መከበር ስለቆሙና ስለጠየቁ ብቻ በገዛ ሃገራቸው ተወልደው ባደጉባት ምድር ላይ እንደጠላት ተፈርጀው ከያሉበት ከየቤታቸው እየተለቀሙ ወደእሥር ቤት ወደ እሥር ቤት ከመወርወራቸውም በላይ በሕሊና እሥረኞቹ ላይ እየደረሰ ያለው ጭካኔ የተሞላበት አረመኔአዊ ድብደባና የሥነ-ልቦና ጥቃት በእጅጉ አሣዝኖናል” ይላል፡፡

ከአዘጋጆቹና ከተሣታፊዎቹ መካከል አንዳንዶቹ “በእሥር ቤት የሚገኙ ወገኖቻችን ብቻቸውን እንዳልሆኑ ለማስታወስም የጠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሥነ-ሥርዓቱ በፀሎትና የሕሊና እሣቤም የታጀበ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት በእሥር ቤት የሚገኙት ሰዎች የታሠሩት በእምነታቸው፣ ወይም በመናገራቸው ወይም በመፃፋቸው ምክንያት ሣይሆን በሽብር አድራጎት በመሣተፋቸው ወይም በማሴራቸው ነው ይላል፡፡

ፀረ-ሽብር ሕጉንና ሥርዓቱን የሚተቹ የሃገር ውስጥ ተቃዋሚዎች እና ዓለምአቀፍ ተቋማት የኢ4ትዮጵያን መንግሥት በሰብዓዊ መብቶች አያያዞቹ በየወቅቱ ሲወቅሱና ሲያወግዙ ይሰማሉ፡፡

ዘገባውን ያዳምጡ
XS
SM
MD
LG