በማሊ መዲና ባማኮ በእስልምና አክራሪዎች ሳይፈጸም አልቀረም በተባለ ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ70 በላይ ሲደርስ፣ ከ200 በላይ የሚሆኑት ላይ ደግሞ ጉዳት ደርሷል።
የማክሰኞው ጥቃት ኢላማ ያደረገው ወታደራዊ ፖሊስ ማሰልጠኛን እና ወታደራዊ የአየር ማረፊያን ነበር ተብሏል።
ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የፀጥታ ምንጭ በጥቃቱ 77 ሰዎች ሲሞቱ 255 ደግሞ መቁሰላቸውን ተናግረዋል።
እውነተኛነቱ የተረጋገጠ ኦፊሴላዊ ሰነድ ደግሞ የሟቾቹን ቁጥር ከ 100 በላይ ነው ይላል። 81 ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት ደርሷል ይላል።
“ሎ ስዋ” የተሰኘው ዕለታዊ ጋዜጣ በዛሬው እትሙ፣ የ50 ወታደራዊ ሠልጣኞች የቀብር ሥነ ሥርዓት መፈጸሙን ዘግቧል።
ከአል ቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለውና ‘እስልምናንና ሙስሊሞችን ደጋፊ ቡድን’ በመባል የሚታወቀው ታጣቂ ሃላፊነቱን በወሰደበት ጥቃት የሞቱትን ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር ወታደራዊው መንግስት እስከአሁን በይፋ አልስታወቀም።
መድረክ / ፎረም