በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የበቆሎ ዋጋ ማሻቀብ በማላዊ የምግብ ዋስትና ላይ ስጋት ደቅኗል


የበቆሎ ዋጋ ማሻቀብ በማላዊ የምግብ ዋስትና ላይ ስጋት ደቅኗል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:11 0:00

የበቆሎ ዋጋ ማሻቀብ በማላዊ የምግብ ዋስትና ላይ ስጋት ደቅኗል

ማላዊ ለዓመታት ከፍተኛ የምግብ እጥረት ባይለያትም፣ አሁን በዩክሬን እየተካሔደ ያለው ጦርነት ኹኔታውን አስከፊ አድርጎባታል። ለዓመታት፣ ከበድ ባለ የምግብ ዋስትና ዕጦት ስትቸገር የከረመችው ማላዊ፣ ባለፈው ዓመት፣ የበቆሎ ዋጋ 110 በመቶ መጨመሩ ግን ሁኔታው ይበልጥ እንዲከፋ አድርጓል።

የምግብ ዋስትና ዕጦቱ የተከሠተው፣ በተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ ችግሮች ምክንያት ነው። ባለፈው የካቲት ሀገሪቱ፣ ‘ፍሬዲ' በተሰኘ አውሎ ነፋስ ስትመታ፣ በደቡብ ክፍል ያለውን በሺሕዎች ሄክታር የሚገመት፣ መሬት ላይ የነበረን ሰብል አውድሟል። በዚኽም ምክንያት፣ ዋናው የዕለት ተዕለት ምግብ ምንጭ የኾነው በቆሎ፣ ባለፈው ነሐሴ 110 በመቶ እንዲጨምር አድርጓል፤ ሲል የቅድመ አደጋ ማስጠንቀቂያ አውታር ያስታውቃል።

ቺምዌምዌ ፓዳታ ከመዲናዋ ሊሎንግዌ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG