ዋሽንግተን —
ላለፉት ስድስት ሣምንታት በተለያዩ የአሜሪካ የትምህርት ተቋማት ሥልጠና አዘል ጉብኝት ሲያደርጉ የቆዩ አንድ ሺህ የሚሆኑ የአፍሪካ ወጣቶች ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ተሰብስበዋል፡፡
ወጣቶቹ ከዩናይትድ ስቴትስ የመንግሥት ሕግ አስፈፃሚ ባለሥልጣናትና ከሕግ አውጭዎቹ እንደራሴዎች ጋር ሲወያዩ ውለዋል።
ይህ በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የተጀመረው መርኃግብር “ማንዴላ-ዋሺንግተን የአፍሪካ ወጣት መሪዎች ተነሳሽነት” ይባላል፡፡
ወጣቶቹ ከአሜሪካ የፖለቲካ፣ የንግድና የማኅበረሰብ መሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡