በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መቀዶኒያ ኔቶን ለመቀላቀል ተፈራረመች


የኔቶ/የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት/ ዋና ፀኃፊ ጂንሰ ስቶልንበርግ እና የመቀዶንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኒኮላ ዲሞትሮቭ
የኔቶ/የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት/ ዋና ፀኃፊ ጂንሰ ስቶልንበርግ እና የመቀዶንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኒኮላ ዲሞትሮቭ

መቀዶኒያ ኔቶን ለመቀላቀል የሚያስችላትን ቁልፍ የሥምምነት ሰነድ ዛሬ ፈርማለች።

መቀዶኒያ ኔቶን ለመቀላቀል የሚያስችላትን ቁልፍ የሥምምነት ሰነድ ዛሬ ፈርማለች። ሂደት በመጪው የአውሮፓውያኑ ዓመት 2020 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ዛሬ ብራሰልስ ውስጥ ፊርማውን በማኖሩ ሥነ ሥርዓት ላይ ከተገኙ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል የኔቶ/የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት/ ዋና ፀኃፊ ጂንሰ ስቶልንበርግ እና የመቀዶንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኒኮላ ዲሞትሮቭ ይገኙበታል።

መቀዶኒያን የኔቶ 30ኛ አባል አድርጎ መቀበል በአካባቢው የበለጠ መረጋጋትና ሴኩዩሪቲ ያስገኛል ብለዋል - የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ ስቶለንበርግ የመቀዶንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኒኮላ ዲሞትሮቭ በበኩላቸው ሃገራቸው ህብረቱን በመቀላቀሏ የምታገኘው ትልቁ ጥቅም ከእንግዲህ በኋላ ብቸኛ አለመሆኗ ነው ብለዋል።

አንዲት ሃገር ጠንካራ ወታደር ካላት የምትጠነክረውን ያህል ዲሞክራሲያዊና ጤናማ ተቋማት ሲኖሯትም ይበልጥ ትጠነክራለች። በተጨማሪ ግን በጠንካራ ወዳጆቿም ትለካለች ሲሉ አስረድተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG