No media source currently available
በአማራ ክልል ምሥራቃዊ አካባቢዎች በበረሃ አንበጣ መንጋ ጉዳት ለደረሰባቸው አርሶ አደሮች የለት ደራሽ የምግብ ድጋፍ ማድረስ ተጀምሯል። አርሶ አደሮቹን በዘላቂነት ለማቋቋም በመስኖ ሥራዎች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ተገልጿል። ደቡብ ወሎ ውስጥ መንጋውን መግታት እንደተቻለና በኦሮሞ ብሔረሰብና በሰሜን ሸዋ ዞኖች ግን በስፋት እየተከሰተ መሆኑን ከየአካባቢው የተገኙ መረጃዎች አመልክተዋል።