በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአንበጣ መንጋ - በምስራቅ አፍሪካ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በአፍሪካ መጠነ ሰፊ ሰብል ያወደመው የአንበጣ መንጋ፣ ምስራቅ አፍሪካ ገጠራማ አካቢዎችን ተመልሶ ማጥቃት እየጀመረ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የምግብና እርሻ ድርጅት/ፋኦ/ ባለስልጣናት ተናገሩ።

ቀደም ሲል ታይቶ በማያውቅ ግዝፈት የከበደ የአምበጣ መንጋ ማዕከላዊና ምስራቅ አፍሪካ ላይ ውድመት ማስከተሉ ይታወቃል። የአሁን በአዲስ መልክ የተነሳው አውዳሚ የአምበጣ መንጋ የተቀሰቀሰው በአለፍ ወር በጣለው ክባድ ዝናብ ጋር ተያይዞ መሆኑን የገለጠው የመንግስታቱ ድርጅት - ባንዳንድ አካባቢዋች ይሄኛው ከፊተኛው ጋር ሲነጻጸር በ20 እጥፍ የሚበልጥ መሆኑን ነው ያመለከተው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG