ዋሽንግተን ዲሲ —
ለአስርተ አመታት የተደረገው ይህ ጥናት የሲጃራን አደገኛነት አረጋግጧል። አንዳንድ ሰዎች በቀን የተወሰነ ምናልባትም አስር ወይም ከዛ ያነሰ ሲጃራን ማጨስ በጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት በጣም አነአስተኛ እንደሆነ በመገመት በሲጃራ ምክንያት የሚከሰቱ በሽታዎች እንደ ሳምባ ካንሰርና ከልብ ጋር ከተያያዙ ህመመሞች የሚይዟቸው አይመስላቸውም።