በሜዲትራኒያን ባሕር በምትገኘው ማለታ ደሴት ያረፈው የሊቢያ አፍሪቂያ አየር መንገድ አውሮፕላን ጠላፊዎች “አውሮፕላኑን በእጅ ቦምብ እናፈነዳለን” ሲሉ ያስፈራሩ ሁለት ተሣፋሪዎች ሳይሆኑ አይቀሩም ሲል አሶሼትድ ፕሬስ የዜና ወኪል ዘገቧል።
ጠላፊዎቹ የአውሮፕላኑን አብራሪ አስቀርተው ሕፃናት፣ ሴቶችን እና ቀሪዎቹን ተሣፋሪዎች እንደለቀቁ የአየር መንገዱ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።
ንብረትነቱ የሊቢያ መንግሥት የሆነው አፍሪቂያ አየር መንገድ አውሮፕላን አንድ መቶ አስራ ስምንት መንገደኞችን ይዞ ከሣብሃ ወደ ትሪፖሊ ከተማ በመብረር ላይ እያለ ነው፤ አቅጣጫውን ወደ ማልታ እንዲቀይር የተገደደው።
የጠላፊዎቹ ማንነትም ሆነ ያቀረቡት ጥያቄ ስለመኖሩ፣ የተገለፀ ነገር የለም።