ዋሺንግተን ዲሲ —
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፌሊፖ ግራንዴ እና የዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት /አይኦኤም/ ዳይሬክተር አንቶንዮ ቪቶሪኖ ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ ነው ያሳሰቡት ።
ሊቢያ ለስደተኞቹ የደኅንነት ዋስትና የማትሰጥ ከሆነ ወደሌሎች ሀገሮች መላክ አለባቸው ብለዋል።
ሁለቱ ባለሥልጣናት አያይዘውም ሜዲቴራንያን ባህር ላይ የሚገኙ ፍልሰተኞች ከእንግዲህ ወደሊቢያ እንዲመለሱ እንደማይደረግ አስታውቋል። ባለፈው ሳምንት ሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ አቅራቢያ በሚገኝ የማቆያ ማዕከል አጠገብ በደረሰ የአየር ጥቃት ከሀምሳ የሚበልጡ ሰዎች መገደላቸው ወደዚያች ሃገር የሚመለሱ ስደተኞች የሚገጥማቸውን አደጋ የሚያሳይ እንደሆኑ ሁለቱ ባለሥልጣናት ገልፀዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ