በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሊቢያው የስደተኞች ማጎሪያ ስድስት ስደተኞ ተገደሉ


ሊቢያ ትሪፖሊ ውስጥ በጸጥታ ኃይሎች ተይዘው በቁጥጥር ስር የሚገኙ ስደተኞች መስከረም 28 2014
ሊቢያ ትሪፖሊ ውስጥ በጸጥታ ኃይሎች ተይዘው በቁጥጥር ስር የሚገኙ ስደተኞች መስከረም 28 2014

ሊቢያ ትሪፖሊ ውስጥ በሚገኘው የስደተኞች ማጎሪያ ጣቢያ ውስጥ በተፈጠረ ቀውስ አብዛኞቹ ስደተኞች ሲያመልጡ፣ ቢያንስ ስድስት የሚሆኑት ደግሞ መገደላቸውን በሊቢያ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ተቋም ተወካይ ትናንት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ከአቅሙ በላይ በስደተኞች በተጨናንቀው “ጎት ሳህል ሴንተር” በሚባለው የማጎሪያው እስር ቤት በተፈጠረው ቀውስ አምልጠው ከወጡት ስደተኞች፣ አብዛኞቹ በጎዳናዎች ላይ ተሰባሰበው እንደሚገኙ ተወካዩ ገልጸዋል፡፡

የሊቢያ ባለሥልጣናት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ስደተኞችን እያሳደዱ ሲሆን ወደ 5ሺ የሚደርሱትን ይዘው ማሰራቸውንም ተወካዩ ገልጸዋል፡፡

በሊቢያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች የሚገኙ መሆኑ በዘገባው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG