በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የክብር ዶ/ር ሎሬት አርቲስት ለማ ጉያ በ92 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ


የክብር ዶ/ር ሎሬት አርቲስት ለማ ጉያ
የክብር ዶ/ር ሎሬት አርቲስት ለማ ጉያ

የክብር ዶ/ር ሎሬት አርቲስት ለማ ጉያ በ92 ዓመታቸው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ሰዓሊ የክብር ዶ/ር አርቲስት ለማ ጉያ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ92 ዓመታቸው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

አርቲስት ለማ ጉያ ላለፉት 65ዓመታት ከ10 ሺህ በላይ ሥዕሎችን በፍየል ቆዳ ላይ በመሳል የሚታወቁ ሲሆን ሥራዎቻቸውንም በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው ለማ ጉያ የሥነ-ጥበብ ማዕከል ውስጥ ለጎብኝዎች ያሳዩ ነበር።

የቀብር ሥነ ስርዓታቸው ሀሙስ በቢሾፍቱ የሚፈፀም መሆኑን ቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን የመገናኛ ብዙሃኑ ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG